46 ሜትር የእንጨት ርብራብ
ወደ አምባው አንድ በር ብቻ — በኹለት እርከን ተከፍሎ 46 ሜትር (አርባ ስድስት) ከፍታ ያለው እንጨት ርብራብ (መሰላል)።

አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
የ14ኛው ክ/ዘመን ታላቅ ኢትዮጵያዊ ሊቅ
ጸሐፊ፣ መምህርና መንፈሳዊ አባት — በ1357 ዓ.ም በወሎ ከላላ ወረዳ ሸግላ (ሰግላ) ተወለዱ። በጥቅምት 3 ተፀንሰው፣ በሐምሌ 7 ተወለዱ። ከአባታቸው የመጀመሪያ ትምህርት በኋላ ወደ ሐይቅ ቅዱስ እስጢፋኖስ — ከአባ ሠረቀ ብርሃን ቤተ-ጉባኤ ተማሩ።
በነሐሴ 21 እመቤታችን ጽውዐ ልቡና አጠጣቻቸው። የንጉሥ ዳዊት ስምንት ልጆች መምህር ሆኑ፤ ማኅሌት ደረሱ። ከአቡነ በጸሎተ ሚካኤል ገዳም ገብተው መነኰሱ — ደብረ ባሕርይ ጋስጫን መሰረቱ።
መጽሐፈ ምስጢር፣ መጽሐፈ ሰዓታትና ሌሎች ብዙ ድርሰቶች — «ብርሃን ኢትዮጵያ» ተብለው ይታወቃሉ። ዋሻ፣ ድልድይና የውኃ ማቈሪያዎች ሠሩ።
በ1417 ዓ.ም በሐምሌ 7 ቀን ዐረፉ። ጌታችን ቃል ኪዳን ሰጣቸው። ሥጋቸው በደብረ ባሕርይ ጋስጫ ገዳም ተቀመጠ — የ600ኛ የእረፍት በዓላቸውን ዛሬም እናከብራለን።

ገዳም በገደል
ደብረ ባሕርይ ጋስጫ
የልብ መመዘኛ ቅዱስ ገዳም
ወደ አምባው አንድ በር ብቻ — በኹለት እርከን ተከፍሎ 46 ሜትር (አርባ ስድስት) ከፍታ ያለው እንጨት ርብራብ (መሰላል)።
ከማያሰርግ ዐለት የተሠሩ — እያንዳንዳቸው ከሁለት ሺህ ሊትር በላይ ውኃ የሚይዙ፤ በቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ተቈፈሩ።
«መዳልወ አልባብ» — የልብ መመዘኛ ቅዱስ ገዳም።
ባሕታውያን የሚገኙበት፣ ጥንታዊ መጻሕፍትና ቅርሶች።
1357 ዓ.ም1417 ዓ.ም
ሰግላ · ከለላ · ወሎ
በቤተ አምራ (አሁን ወሎ) በከለላ ወረዳ ሸግላ (ሰግላ) ተወለዱ። በጥቅምት 3 ቀን 1357 ዓ.ም ተፀንሰው፣ በሐምሌ 7 ተወለዱ። አባታቸው ሕዝበ ጽዮን — የቤተ መንግሥት ባለሟል፣ ጠቢብና የሰግላ ሀገረ ገዥ — እናታቸውም እምነ ጽዮን ናቸው። ሁለቱም እንደ ዘካርያስና ኤልሳቤጥ በእግዚአብሔር ሕግ ጸንተው ሲኖሩ ልጅ አልነበራቸውም። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከመልአኩ ቅዱስ ዑራኤል ጋር ተገልጻ ጸሎታቸውን ተቀብላ የተባረከ ልጅ እንደሚወልዱ፣ ስሙንም እንደ ሰማእታት አለቃ ቅዱስ ጊዮርጊስ «ጊዮርጊስ» እንዲሰይሙ አዘዘቻቸው።
ሰግላ · ሐይቅ እስጢፋኖስ
የመጀመሪያ ትምህርታቸው ከአባታቸው ሕዝበ ጽዮን ነበር። በአፄ ዳዊት ዘመን መጀመሪያ አካባቢ ወደ ጳጳስ አቡነ ሰላማ መተርጉም ወስደው ዲቁና ማዕረግ አሾሟቸው። ከዚያም በንጉሥ ዳዊት ዘመን (1378 - 1405 ዓ.ም) ወደ ሐይቅ ቅዱስ እስጢፋኖስ ገዳም ሄደው ከታላቁ ሊቅ ዓቃቤ ሰዓት አባ ሠረቀ ብርሃን ቤተ-ጉባኤ ተማሩ። የቀለም ትምህርት ቶሎ አልያዙም — ከትምህርት ይልቅ የገዳሙን አበው መርዳትና የብሕትውናን ሕይወት ይመርጡ ነበር። ጓደኞቻቸው ሲቀድሟቸው አዝነው በእንባና በጾም ከእመቤታችን ሥዕል ፊት ጥበብን ለመኑ።
ወላዲተ አምላክ
እመቤታችን ወላዲተ አምላክ በነሐሴ 16 ቀን ተገልጻ ራሳቸውን እንዲያነጹ፣ ነፍሳቸውን እንዲቀድሱና ቀጠሮ እንዲጠብቁ አዘዘቻቸው። በነሐሴ 21 ቀን ከኪሩቤል፣ ሱራፌልና መላእክት ጋር ተመልሳ መጣች። ቅዱስ ሚካኤል በቀኟ፣ ቅዱስ ገብርኤል በግራዋ ቀረቡ። እመቤታችን ከእውቀት ወንዝ የመጣ ንጹሕ ጽዋ አጠጣቻቸው — ያ ጽዋ ጽውዐ ልቡና ነው። የሰማይና የምድር ምስጢር ተገለጸላቸው፤ በእግዚአብሔር ፈቃድ ቤተ ክርስቲያን የምትገለገልባቸው ብዙ ቅዱሳን መጻሕፍትን ደረሱ።
ዓፄ ዳዊት
ዓፄ ዳዊት ሊቅነታቸውን አውቀው ወደ ቤተ መንግሥት አስጠርተው ከበረሯቸው። የስምንቱ ልጆቻቸው መምህር አደረጓቸው — ከነሱም ቅዱስ የተባለው ንጉሥ ቴዎድሮስ፣ እንድርያስ፣ ይሥሐቅ፣ ንግሥት እሌኒና ዘርአ ያዕቆብ ይገኛሉ። ለነገሥታት፣ ካህናትና መሳፍንት አስተማሪ ሆኑ። ማኅሌት ደረሱ፤ ከጋርማዊው አቡነ ሳሙኤል ዜማን ተምረዋል። ዓፄ ዳዊት በጋብቻ ሊያስሹዋቸው ፈልገው ነበር — እሳቸው ግን የመንግሥተ ሰማያት ጃንደረባ ማድረግን መረጡ።
በጸሎተ ሚካኤል · ዓፄ ይሥሐቅ
የአመክሮ ጊዜያቸውን ሲጨርሱ ከታላቁ አቡነ በጸሎተ ሚካኤል ገዳም ገብተው መነኰሱ። በማኅበሩ ራስ ሆነው ደብረ ባሕርይ ጋስጫ ገዳምን መሰረቱ — የተመሠረተበት ዘመን ከአስተማሯቸው ነገሥታት በአንዱ በዓፄ ይሥሐቅ ዘመን ነው። ዋሻ ቤተ ክርስቲያን ፈልፍለው፣ የውኃ ማቈሪያዎች ቈፈሩ፣ ድልድይ ሠሩ። በትምህርታቸው የተመሠጡ ሊቃውንት «ዳግማይ ዮሐንስ አፈወርቅ» ሲሏቸው፣ ዓፄ ይሥሐቅም «ኢትዮጵያዊው ቄርሎስ» ብለው ሰይመዋቸዋል።
ብርሃን ኢትዮጵያ
መጽሐፈ ምስጢር፣ መጽሐፈ ሰዓታት፣ አርጋኖን፣ ውዳሴ መስቀል፣ መጽሐፈ ፈውስ፣ መጽሐፈ ባሕርይና ሌሎች ብዙ ድርሰቶች ጻፉ። መጽሐፈ ምስጢር ከእረፍታቸው በፊት በሁለት ዓመት አካባቢ ተጠናቀቀ። በገድላቸው «ብርሃን ኢትዮጵያ» እና «ያሬድ ሁለተኛ» ተብለው ይታወቃሉ — እስከ ዛሬም በሀገራችን አምሳያ የላቸውም።
ሐምሌ 7 · ጋስጫ
ቆመው እየጸለዩ ሳሉ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእመቤታችንና ከቅዱሳን ጋር ተገልጦ ቃል ኪዳን ሰጣቸው — የገዳሙን ልጆች፣ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች፣ የገድሉን ጸሐፊዎችና አድማጮች እንደሚምራቸው። በስድሳኛው ዓመታቸው በ1417 ዓ.ም በሐምሌ 7 ቀን ዐረፉ። ቅድስት ነፍሳቸው በይባቤ መላእክት ዐረገች፤ ደቀ መዛሙርትም ሥጋቸውን በደብረ ባሕርይ ጋስጫ ገዳም አኖሩ።
ቅዱስ ቀናት
ዓመታዊ በዓላት — ለጸሎት፣ ለመታሰቢያና ለምስጋና።
ሁሉንም በዓላት01
የተፀነሱበት ቀን
02
ልደት እና እረፍት
03
ጽውዐ ልቡና

600ኛበዓለ እረፍት
ቅዳሜ ነሐሴ 30 2018 ዓ.ም
ከቀኑ 7 ሰዓት ጀምሮ
ቦሌ ደብረ ሳሌም መዳኃኔዓለምመጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ወአቡነ አረጋዊ ካቴድራል