ንጉሥ
ሰይፈ አርዕድ
የተወለዱት በአጼ አምደ ጽዮን የመጀመሪያ ልጅ — አጼ ነዋየ ክርስቶስ፣ ሰይፈ አርዕድ — ዘመን ነው። የነገሡት በ1337 ዓ.ም ሲሆን አባ ጊዮርጊስ ሲወለዱ ከንግሥናቸው ሃያ ዓመት አልፎ ነበር። አስታራቂና ጥበበኛ ንጉሥ — በአባታቸው ዘመን የታሰሩ መነኮሳትን ከእስር ፈትተው ከቤተ ክርስቲያን ጋር ሰላም መሠረቱ።
ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
የ14ኛው ክ/ዘመን ታላቅ ኢትዮጵያዊ ሊቅ
የወርቃማው ዘመን ወርቃማ ደራሲ መናኝ ጻድቅ የህዝብ መምህርና የስነ ምህንድስና ባለሙያ የሆነው ኢትዮጵያዊው ሊቅ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ የተወለዱት በ1357 ዓ.ም በቤተ አምራ በአሁኑ ወሎ ክፍለ ሀገር በከለላ ወረዳ ሸግላ (ሰግላ) በተሰኘች ቦታ ሲሆን አባታቸው ሕዝበ ጽዮን እናታቸው እምነ ጽዮን ይባላሉ።
የነበሩበት ዘመን
ከተወለዱበት እስከ ዐረፉበት ያለው ዘመን ስድሳ ዓመት ነው። ያ ዘመን የሊቃውንት፣ የትርጓሜና የዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘመን ነበር።
ንጉሥ
የተወለዱት በአጼ አምደ ጽዮን የመጀመሪያ ልጅ — አጼ ነዋየ ክርስቶስ፣ ሰይፈ አርዕድ — ዘመን ነው። የነገሡት በ1337 ዓ.ም ሲሆን አባ ጊዮርጊስ ሲወለዱ ከንግሥናቸው ሃያ ዓመት አልፎ ነበር። አስታራቂና ጥበበኛ ንጉሥ — በአባታቸው ዘመን የታሰሩ መነኮሳትን ከእስር ፈትተው ከቤተ ክርስቲያን ጋር ሰላም መሠረቱ።
ጳጳስ
በዚያ ዘመን መጀመሪያ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ያዕቆብ ነበሩ። ከዚያም አቡነ ሰላማ መተርጉም መጡ — ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ማዕረገ ዲቁና የተቀበሉት በዚህ ትውፊት ውስጥ ነው።
ዓለም
ሰይፈ አርዕድ ከኢትዮጵያ አልፈው በግብጽ የእስክንድርያ ቆጦች ጠባቂ ተብለው ይታወቃሉ። ፓትርያርክ ማርቆስ 4ኛ በሱልጣን ሲታሰሩ ንጉሡ እስከ አስዋን ድረስ ሠራዊት አዘመቱ — ፓትርያርኩም ተፈቱ። አባ ጊዮርጊስ በዚህ ክፍት ዘመን ተወለዱ።
፯ ነጥቦች
አንድ ሕይወት · ብዙ ጥበብ
የሥነ ጽሐፍ ደራሲ ብቻ አይደሉም — ዜማ፣ ቅዳሴ፣ ሕንጻ፣ ፈለክና ሥርዓተ ማኅበር በአንድ ሕይወት ውስጥ ተገናኙ።
ጥቂት ቢኖር እወዳለሁ
አፄ ዳዊት አባ ጊዮርጊስ የጻፉትን መጽሐፈ አርጋኖን በወርቅ ቀለም እስከ ማጻፍ የደረሱ የቅዱሱ አባት ወዳጅ ነበሩ።
በኋላ ግን ቢቱ የተባለ መናፍቅ በሐሰት ክስ አጣላቸውና አፄ ዳዊት የቢቱን ቃል አምነው አባ ጊዮርጊስን በደም እስኪሸፈኑ አስገርፈው ንጹሑን አባት በግፍ ወደ እስር ቤት አስወረወሩ።
ከጥቂት ጊዜ በኋላ በእስር ቤት ሆነው ሳለ አፄ ዳዊት አርፈው ልጃቸው ቴዎድሮስ ቀዳማዊ እንደነገሠ ሲሰሙ እጅግ አዘኑ። ወዳጆቻቸውም «ያን ሁሉ ግፍ ያደረሰብዎት ንጉሥ ሞተ ሲባሉ ሊደሰቱ ሲገባ ስለ ምን ያዝናሉ?» ብለው ጠየቁ።
«እመቤታችንን የሚወድ ሰው ነውና ጥቂት ቢኖር እወዳለሁ።»
#አርጋኖን
በመጽሐፈ አርጋኖን ውስጥ ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ስለ ኃጢአት፣ ስለ እመቤታችን ጸጋና ስለ ምሕረት የተጻፉ ጸሎቶች አሉ።
1 / 12
እመቤታችንን ስለ ግብፅ መከራና ስለ ልጇ ጸጋ ለንስሐ ያስታውሳሉ።
ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ስለ እመቤታችን በጸሎታቸው እነዚህን መርሆዎች ያስቀምጣሉ፦
እመቤታችንን ከሁሉ ኃጢአት ይልቅ ከመውደድ፣ ከልጇና ከመንፈስ ቅዱስ እምነት በቀር ሌላ ትሩፋት እንደሌላቸው ይቅር እንዲሰጡ ይለምናሉ።
እመቤታችን የምሕረት ፈሳሽ ምንጭ ስለሆኑት ልጇ ኃጢአታቸውን እንዳያስብብላቸው ይጸልያሉ።
በኃጢአት ሁሉ እንደ እነሱ ያለ በደለኛ የለም፣ ልጇም ቸር ይቅር ባይ ከመዓት የራቀ እውነተኛ ምሕረት የለም በማለት ይመሰክራሉ።
እመቤታችን ከተወለዱ ጀምሮ ሰይጣን እረፍት አላገኘም፣ በእርሳቸው ታመመ፣ በልጇም ተጨነቀ — ስለዚህ ሰይጣን እመቤታችንን ከሁሉ ይጠላል በማለት ይገልጻሉ።
በመጽሐፋቸው ስለ ንስሐ እንዲህ ይገልጻሉ — ኃጢአታቸው ሊከሰኝ ይጮኻል፣ ለምን ዝም እንደሚሉና የሠራሉት ክፉ ሥራ እንደሚያሳጣቸው ይናገራሉ።
ኃጢአታቸው ከራሳቸው ፀጉር በዝቶ እንደ ጽኑ ሸክም እንደሚከብዳቸው ይገልጻሉ።
ስለ ኃጢአታቸው ራሳቸውን ወደ ልዑል እግዚአብሔር እንደሚያቀርቡ ይማረማረራሉ።
600ኛ ዓመት
60
ስድሳ
ዓመት ሥራ
600
ስድስት መቶ
ዓመት ብርሃን
ቅዱስ አባታችን በ1417 ዓ.ም በሐምሌ 7 ቀን ዐረፉ። በረከተ ጸሎታቸው ከሁላችን ጋር ይኑር — አሜን